አልፋ መረጃ
40 ሺህ ዜጎችን የመመለሱ ዘማቻ ተጀመረ። በሳውዲ ዐረቢያ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ያሉ ዜጎችን ከትላንት ሌሊት ጀምሮ መመለስ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ እስረኞችን ወደ ሀገር የመመለስ ዘመቻውን በተመለከተ ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የሰጡት መረጃ፦ - ዛሬ ከጅዳ 4 እና ከሪያድ 2 አውሮፕላኖች በጥቅሉ 6 አውሮፕላኖች ታሳሪዎችን ወደ ሀገር መመለስ ይጀምራሉ። - ለአሁኑ በረራ በእስር ቤቶች ዉስጥ ያሉ ሴቶች፣ህጻናትና አቅመ ደካሞች ተመርጠዋል። - ቀጥሎም በየቀኑ 8 በረራዎችን በማድረግ 40 ሺ ታሳሪዎችን በ2 ሳምንት ዉስጥ ወደ ሀገር ለመመለስ ታቅዷል። - ከዛሬ ጀምሮ በሁለት ሳምንት ዉስጥ ወደ ሀገር የሚመለሱት ቀደም ብለው በተለያዩ እስር ቤቶች ዉስጥ ታስረው የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንን እንጂ ሰሞኑን እየታሰሩ ያሉትን አይጨምርም። - ሰሞኑን በአፈሳ መልኩ እየታሰሩ የሚገኙትን አስመልክቶ በድንገት የተያዙ ስለሆነ በሳውዲ ዐረቢያ ቆይታቸው ያፈሩት ሀብትና ንብረት ያላቸው በመሆኑ ሀብትና ንብረቶቻቸውን ሳይወስዱ ባዶ እጃቸውን ወደ ሀገር መመለስ የለባቸውም ብለው ለሳውዲ ዐረቢያ መንግስት አቤቶታ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው። ከፊሎቹ ደግሞ የገንዘብ ቅጣት ሳይከፍሉ ከሳውዲ መውጣት የማይችሉ በመሆናቸው የገንዘብ ቅጣቱ ምህረት እንዲደረግላቸው እየተጠየቀ ነው። - ሰሞኑን በአፈሳ የተያዙ ዞጎች ጉዳይ አሁን ወደ ሀገር ለመመለስ የተዘጋጁት 40ሺህ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ዘመቻ ሲጠናቀቅ የሚቀጥል ነው። ይህን መረጃ ከኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተገኘ ነው።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ