ቅዳሜ, ጁላይ 24, 2021

ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።


 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ለመጣሏ የመልስ ምት ነው።

አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥላ የነበረው በዜጎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ እጃቸው አለበት በሚል ነበር።

አሁን ቻይና ማዕቀብ ከጣለችባቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መካከል የቀድሞው የንግድ ዘርፍ ጸሐፊ ዊልበር ሮስ በዋ ዋንኝነት ይጠቀሳሉ።

ከዊልበር ሮስ በተጨማሪ የመብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች የቻይና ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሶፊ ሪቻርድሰን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

የቻይና እና አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና ደኅንነት ኮሚሽን ኃላፊ ካሮሊን ባርቶሎሜው፣ የዓለም አቀፉ የሪፐብሊካን ተቋም አመራር አዳም ኪንግ ላይም ማዕቀብ ተጥሏል።

የአሁኑ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዌንዲ ሸርማን በጥቂት ቀናት ውስጥ ቻይናን ይጎበኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው ፥ በዚህ ወቅት ነው እንግዲ ቻይና በአሜሪካ ባለስጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል የጀመረችው።

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ አሜሪካ በቻይና ማዕቀብ "አትበገርም" ብለዋል።

NB : ቻይና ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ማይክ ፖምፕዮን ጨምሮ 27 የትራምፕ ዘመን አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ...