#Update
ትላንት የተከዜ ድልድይ መውደሙ መግለፁ አይዘነጋም።
ከድልድዩ መውደም በኃላ ሁኔታው ወደትግራይ ለሚደረገው ለእርዳት አቅርቦት የሚፈጥረውን ትልቅ እንቅፋት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል።
IRC፣ WFPና OCHA ስለድልድዩ መፍረስ ያሉትን ትላንት በ#TigrayReport መረጃ ተለዋውጠናል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ በፌዴራል መንግስት ስር ያለው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ" ድልድዩ የፈረሰው በህወሓት መሆኑን ገልጿል።
"የትግራይ አርሶአደሮች የመህር ግብርና እንዲያከናውኑ ለመደገፍ የወጣውን የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ውድቅ ያደረገው ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የተከዜ ድልድይን ሆን ብሎ ወደክልሉ የሚወስደውን የእርዳታ መስመር ለመገደብ አውድሟል" ሲል ፅፏል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ