የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ከምርጫ ቦርድ መግለጫ የተወሰዱ‼️
1. ኮሞና ምርጫ ክልል (ኦሮሚያ)
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ አለው
- 150, 829 በመራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- በብቸኝነት የተወዳደረው የብልጽግና ፓርቲ 3 ዕጩዎች አሸንፈዋል
2. ሀብሮ 2 ምርጫ ክልል
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ አለው
- በ38 ምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ 50, 966 ሲሆኑ 50, 281 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- በ3ቱም የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ብልጽግና አሸንፏል
- በምርጫ ክልል የተወዳደረው 1 ፓርቲ ብቻ ነው
4. ምርጫ ክልል ጭሮ 2
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች አሉት
- የምርጫ ጣቢያዎች ብዛት 44
- የተመዘገቡ መራጮች ብዛት 62, 521
- በመራጮች መዝገብ ላይ የፈረሙት 62, 504
- ለ3ቱም መቀመጫዎች የቀረቡት ዕጩዎች ከብልጽግና ፓርቲ ሲሆኑ አሸንፈዋል
5. የምርጫ ክልል ስያሜ ጮራ
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 106 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 72, 816 መራጮች ተመዝግበዋል። 72, 497 ሰዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- ሶስቱን መቀመጫዎችን ብልጽግና አሸንፏል። የኢዜማ ዕጩ 4ኛ ድምጽ አግኝተዋል
6. ሌመን ምርጫ ክልል
- ሶስት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 80 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 46,095 መራጮች ተመዝግበዋል
- በሶስቱም የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና አሸንፏል
- ዕጩዎች ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው
7. መሰላ ምርጫ ክልል
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 77 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 112, 254 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡ 107, 905 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- ብልጽግና ፓርቲ 3ቱንም መቀመጫዎች አሸንፏል
- ዕጩዎች ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው
8. በኦሮሚያ ክልል የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልል ጭሮ ሶስት
- 54, 845 መራጮች ተመዝግበዋል
- 54, 813 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- በምርጫ ክልሉ ብልጽግና አሸንፏል
- ዕጩው ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው
9. የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ጎማ ሁለት
- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 85 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 79,275 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡ 78,198 በመዝገብ ላይ ፈርመዋል
- 3ቱን መቀመጫዎች ብልጽግና አሸንፏል
- ዕጩዎቹ ከ1 ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው
10. ለተወካዮች ምክር ቤት በደሌ ምርጫ ክልል
- 114 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 117, 143 መራጮች ተመዝግበዋል
- በምርጫ ክልሉ ብልጽግና አሸንፏል
- በምርጫ ክልሉ የተወዳደረው አንድ ፓርቲ ብቻ ነው
11. አማራ ክልል ጢስ አባይ ምርጫ ክልል (ለተወካዮች ምክር ቤት)
- 74 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት
- 48, 834 መራጮች ተመዝግበዋል
- 24, 829 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል
- በዚህኛው ምርጫ ክልል አብን አሸንፏል
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ