ቅዳሜ, ጁን 26, 2021

 የዝነኛው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው ሙሉ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል ብለዋል።

ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ፥ የፊታችን ሰኞ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ በ34 ዓመቱ ከተገደለ 1 ዓመት እንደሚሆነው አስታውሰዋል። አክለውም ፥ "ህዝቡ ለእሱ ያለውን ስሜት አውቃለሁ፤ ድምፁን መስማት ያፅናናቸዋል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። ወ/ሮ ፋንቱ የድምፃዊ ሃጫሉ አዲሱ (3ኛው) አልበም ከመሞቱ ብዙም ሳይቆይ በፊት የተቀዱ ስራዎች እንዳሉት ተናገረዋል። አዲሱ አልበም "Maal Mallisaa" የሚሰኝ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙ "መፍትሄው ምንድነው ?" የሚል ነው። በነገራችን ላይ አልበሙ በቀጣይ ሳምንት ለገበያ የሚቀርብ ቢሆንም ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ በ iTunes ላይ ቀርቧል ፤ እዛ ላይ በመግዛት ማዳመጥ ይቻላል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ አልበሙ በCD አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለገበያ ይቀርባል። ውድ የቲክቫህ አባላት አልበሙን ህጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ በመግዛት እንድታዳምጡ እናበረታታለን፤ በማህበራዊ ሚዳያዎች ላይ በህገወጥ መንገድ እንዳይሰራጭ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ አድርጉ። ድምፃዊ ሃጫሉ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ ይታወሳል።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ...