የMSF ባልደረቦች የተገደሉት በህወሓት ኃይሎች ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ገለፀ።
መንግስት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጣው መግለጫ ፥ አቢ አዲ በተባለ ስፍራ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኛ በሆኑ 3 ሰዎች ላይ ግድያ ተፈፅሟል፤ ግድያውን የህወሓት የሽብረ ቡድን አባላት ናቸው የፈፀሙት" ብሏል። በዚህም ሀዘን እንደተሰማውና ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንደሚመኝ ገልጿል። በዚሁ ሃዘን መግለጫ መንግስት በተደጋጋሚ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የፀጥታ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ለሰራተኞች ደህንነት ሲባል ማንኛውም እንቅስቃሴ በመከላከያና በፀጥታ አካላት ታጅበው ለዜጎች እንዲያደርሱ ሲመክር መቆየቱ አስታውሷል። ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የተወሰኑ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶቾ ከመንግስት እውቅና ውጪ ሲንቀሳቀሱ ይስታዋላል ይህም የከፈ ችግር እያስከተለ ነው ብሏል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አብይአዲ አካባቢ ህወሓት እንደሚንቀሳቀስ በመግለፅ በአካባቢው 3 የMSF ሰራተኞች ባልደረቦች ገልጿል። ሰራዊቱ ፥ "የበለጠ በራሳችን መንገድ የሚረጋገጥ ቢሆንም ፥ የህወሓት ታጣቂዎች ሰራተኞቹን ከመኪና አስወርደው እንደገደሏቸው ቅድመ መረጃ ደርሶናል" ብሏል። ከሟቾቹ መካከል አንዷ ስፔናዊት ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ገልጿል። በቀጣናው እርዳታ ሰራተኞች እንዲሁም ሚዲያ አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ሲያሳስብ እንደነበር አስታውሷል። ሰራዊቱ የሟቾችን አስክሬን በክብር እንዲያርፍ ለማድረግ ፣ ለሚያጣራ አካልም ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍል ገልጾ፤ በራሱ በኩልም ጠንካራ ማስረጃ አስደግፎ እንደሚያቀርብ ቃል ገብቷል። ወንጀለኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።
ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ...
-
#FDREDefenseForce የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ይገኛል። ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ወቅት ለውትድርና ሙያ ብቁ የሚያደርጋቸውን ...
-
የእነ ጀነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጣ። የእነ ጀነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። አቃቤ ህግ በሞት እንዲቀጣ ጥያቄ አ...
-
#Update ትላንት የተከዜ ድልድይ መውደሙ መግለፁ አይዘነጋም። ከድልድዩ መውደም በኃላ ሁኔታው ወደትግራይ ለሚደረገው ለእርዳት አቅርቦት የሚፈጥረውን ትልቅ እንቅፋት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲገለፅ እንደነበር ይታወ...
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ