ሰኞ, ጁን 28, 2021

አሜሪካ የአየር ድብደባ ፈፀመች።

 አሜሪካ የአየር ድብደባ ፈፀመች።

አሜሪካ በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎችን ዒላማ ያደረገ የአየር ድብደባ በኢራቅ እና በሶሪያ ውስጥ መፈጸሟን የመከላከያ መሥሪያ ቤቷ ፔንታገን አስታወቀ። ጥቃቱ ሚሊሻዎቹ በአሜሪካ ወታደሮች ሰው አልባ አውሮፕላን ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ምላሽ "በጦር መምሪያ እና በጦር መሣሪያ ማከማቻ ተቋማታቸው ላይ" የተፈጸመ ነው ተብሏል። "ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካን ወታደሮችን ለመጠበቅ እርምጃ እንደሚወስዱ ግልጽ ነው" ብሏል ፔንታገን። ጆ ባይደን ስልጣን ከያዙ ወዲህ በኢራን በሚደገፉ ሚሊሻዎች ላይ የአየር ድብደባ እንዲፈጸም ሲፈቅዱ ይህ ሁለተኛው ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት መቀመጫቸውን ኢራቅ ባደረገው የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተሰንዝሮባቸዋል። ኢራን በጥቃቶቹ እጇ እንደሌለበት ገልጻለች። 2,500 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች አይ ኤስ የሚዋጋ ዓለም አቀፍ ጥምረት አካል ሆነው ኢራቅ ውስጥ ይገኛሉ። ፔንታገን ፥ በመከላከያ ዒላማቸውን በጠበቁ የአየር ጥቃቶች በሶሪያ ውስጥ 2 ፤ 1 ደግሞ በኢራቅ ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎች ተመተዋል ብሏል፡፡ ካታብ ሂዝቦላህ እና ካታይብ ሰይድ አል ሹሃዳን ጨምሮ በኢራን የሚደገፉ የሚሊሺያ ቡድኖች ዒላማ የተደረትን ተቋማት ይጠቀሙባቸዋል ተብሏል። አሜሪካ እአአ ከ2009 ጀምሮ ካታይብ ሂዝቦላህ የኢራቅን ሠላምና መረጋጋት አደጋ ላይ ጥሏል በሚል በሽብርተኛነት ፈርጃለች። የፔንታገን መግለጫ አሜሪካ ራሷን በመከላከል እርምጃ ወስዳለች ብሏል። አደጋ ለመገደብ የታቀደ "አስፈላጊ፣ ተገቢ እና ሆን ተብሎ የተወሰደ እርምጃን ወስዳለች። ግልጽና ግልጽ ያልሆነ መልዕክት ለመማስተላለፍም ነው" ብሏል።
አሜሪካ በኢራቅ እና በሶሪያ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ድብደባ የሰዎች ህይወት አልፏል። ኤሜሪካ በፈፀመችው የአየር ድብደባ አምስት ሚሊሻዎች ሶሪያ ውስጥ ስለመገደላቸው ሶሪያን ኦብዘርቫቶሪ ፎር ሒውማን ራይትስ አሳውቋል። የሶርያ የመንግሥት የዜና ወኪል (ሳና) በበኩሉ አንድ ህጻን መሞቱን እና ቢያንስ 3 ሰዎች መቁሰላቸውን ዘግቧል። መረጃው የኤኤፍፒ / ቢቢሲ ነው።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ...