ቅዳሜ, ጁላይ 24, 2021

ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።


 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ለመጣሏ የመልስ ምት ነው።

አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥላ የነበረው በዜጎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ እጃቸው አለበት በሚል ነበር።

አሁን ቻይና ማዕቀብ ከጣለችባቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መካከል የቀድሞው የንግድ ዘርፍ ጸሐፊ ዊልበር ሮስ በዋ ዋንኝነት ይጠቀሳሉ።

ከዊልበር ሮስ በተጨማሪ የመብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች የቻይና ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሶፊ ሪቻርድሰን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

የቻይና እና አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና ደኅንነት ኮሚሽን ኃላፊ ካሮሊን ባርቶሎሜው፣ የዓለም አቀፉ የሪፐብሊካን ተቋም አመራር አዳም ኪንግ ላይም ማዕቀብ ተጥሏል።

የአሁኑ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዌንዲ ሸርማን በጥቂት ቀናት ውስጥ ቻይናን ይጎበኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው ፥ በዚህ ወቅት ነው እንግዲ ቻይና በአሜሪካ ባለስጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል የጀመረችው።

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ አሜሪካ በቻይና ማዕቀብ "አትበገርም" ብለዋል።

NB : ቻይና ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ማይክ ፖምፕዮን ጨምሮ 27 የትራምፕ ዘመን አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ይገኛል።

 #FDREDefenseForce

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ይገኛል።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ወቅት ለውትድርና ሙያ ብቁ የሚያደርጋቸውን የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ወስደው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

በምርቃት ስነስርቱ ላይ የተገኙት የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ለተመራቂ ወታደሮቹ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ጀኔራል መኮንኖች፣ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮ/ል አዲሱ ተርፋሳ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል ፤ ከሀገር መከላከያ እና ለኢዜአ እንደተገኘው መረጃ።

NB : የሁርሶ የሰላም ማስከበር ማዕከል በምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ እና አንጋፋ ከሚባሉት ማሰልጠኛዎች መካከል ተጠቃሽ ነው።


ሰለሞን ቱፋ ለ ነሀስ 🥉 ሜዳሊያ ይወዳደራል !

 ሰለሞን ቱፋ ለ ነሀስ 🥉 ሜዳሊያ ይወዳደራል !

የጃፓኑን ተጋጣሚው ሰርጅዮ ሱዙኪ በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፈው ሰለሞን ቱፋ ደምሴ በቱኒዚያው ተፎካካሪው በነጥብ ልዩነት ቢሸነፍም በተሻለ ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ተጫማሪ ውድደሩን ያደርጋል።

ሰለሞን ቱፋ ዛሬ ከ ቀኑ 7:15 ላይ ከ ሩሲያዊው አርታሞኖቭ ሚኪሀሊ ጋር የሚፋለም ይሆናል።

ሰለሞን ቱፋ የነሀስ ሜዳልያ ለማግኘት በሚደረገው ፉክክር ከሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተወዳዳሪ አርታሞኖቭ  ሚካዪል ጋር የሚፋለም ይሆናል፡፡

መልካም እድል ለሀገራችን ልጅ ሰለሞን ቱፋ !


ዓርብ, ጁላይ 02, 2021

ትላንት የተከዜ ድልድይ መውደሙ መግለፁ አይዘነጋም።

 #Update


ትላንት የተከዜ ድልድይ መውደሙ መግለፁ አይዘነጋም።


ከድልድዩ መውደም በኃላ ሁኔታው ወደትግራይ ለሚደረገው ለእርዳት አቅርቦት የሚፈጥረውን ትልቅ እንቅፋት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል።


IRC፣ WFPና OCHA ስለድልድዩ መፍረስ ያሉትን ትላንት በ#TigrayReport መረጃ ተለዋውጠናል።


በዛሬው ዕለት ደግሞ በፌዴራል መንግስት ስር ያለው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ" ድልድዩ የፈረሰው በህወሓት መሆኑን ገልጿል።


"የትግራይ አርሶአደሮች የመህር ግብርና እንዲያከናውኑ ለመደገፍ የወጣውን የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ውድቅ ያደረገው ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የተከዜ ድልድይን ሆን ብሎ ወደክልሉ የሚወስደውን የእርዳታ መስመር ለመገደብ አውድሟል" ሲል ፅፏል።




ሐሙስ, ጁላይ 01, 2021

የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ከምርጫ ቦርድ መግለጫ የተወሰዱ‼️

 የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ከምርጫ ቦርድ መግለጫ የተወሰዱ‼️


1.  ኮሞና ምርጫ ክልል (ኦሮሚያ)

-  3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ አለው 

- 150, 829 በመራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል 

- በብቸኝነት የተወዳደረው የብልጽግና ፓርቲ 3 ዕጩዎች አሸንፈዋል 


2. ሀብሮ 2 ምርጫ ክልል 

- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ አለው

- በ38 ምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ 50, 966 ሲሆኑ 50, 281 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል

- በ3ቱም የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ብልጽግና አሸንፏል

- በምርጫ ክልል የተወዳደረው 1 ፓርቲ ብቻ ነው


4. ምርጫ ክልል ጭሮ 2

- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች አሉት

- የምርጫ ጣቢያዎች ብዛት 44

- የተመዘገቡ መራጮች ብዛት 62, 521 

- በመራጮች መዝገብ ላይ የፈረሙት 62, 504 

- ለ3ቱም መቀመጫዎች የቀረቡት ዕጩዎች ከብልጽግና ፓርቲ ሲሆኑ አሸንፈዋል


5. የምርጫ ክልል ስያሜ ጮራ

- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 106 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት

- 72, 816 መራጮች ተመዝግበዋል። 72, 497 ሰዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል

- ሶስቱን መቀመጫዎችን ብልጽግና አሸንፏል። የኢዜማ ዕጩ 4ኛ ድምጽ አግኝተዋል


6.  ሌመን ምርጫ ክልል

- ሶስት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 80 ምርጫ ጣቢያዎች  አሉት

- 46,095 መራጮች ተመዝግበዋል

-  በሶስቱም የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና አሸንፏል

- ዕጩዎች ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው


7.  መሰላ ምርጫ ክልል 

- 3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 77 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት

- 112, 254 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡ 107, 905 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል

-  ብልጽግና ፓርቲ 3ቱንም መቀመጫዎች አሸንፏል

- ዕጩዎች ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው


8. በኦሮሚያ ክልል የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልል ጭሮ ሶስት

-  54, 845 መራጮች ተመዝግበዋል

- 54, 813 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል

- በምርጫ ክልሉ ብልጽግና አሸንፏል

-  ዕጩው ከአንድ ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው


9. የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ጎማ ሁለት

-  3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 85 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት

-  79,275 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡ 78,198 በመዝገብ ላይ ፈርመዋል

-  3ቱን መቀመጫዎች ብልጽግና አሸንፏል

- ዕጩዎቹ ከ1 ፓርቲ ብቻ የቀረቡ ናቸው


10.  ለተወካዮች ምክር ቤት በደሌ ምርጫ ክልል

- 114 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት

- 117, 143 መራጮች ተመዝግበዋል

- በምርጫ ክልሉ ብልጽግና አሸንፏል

- በምርጫ ክልሉ የተወዳደረው አንድ ፓርቲ ብቻ ነው


11. አማራ ክልል ጢስ አባይ ምርጫ ክልል (ለተወካዮች ምክር ቤት)  

- 74 ምርጫ ጣቢያዎች አሉት

- 48, 834 መራጮች ተመዝግበዋል

- 24, 829 መራጮች መዝገብ ላይ ፈርመዋል

- በዚህኛው ምርጫ ክልል አብን አሸንፏል



ሰኞ, ጁን 28, 2021

በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጀመረ።

በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጀመረ። ዛሬ በተጀመረው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ735 የፈተና መስጫ ማዕከላት 44,144 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። ፈተናው ሰኔ 23 የሚጠናቀቅ ሲሆን በፈተናው ፈታኞች ፣ ተቆጣጣሪዎች ፥ ፖሊሶችን ጨምሮ 2,778 የሚሆኑ አካላት ተሳታፊ መሆናቸውን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት አሳውቋል።



አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ጸረ ሽብርና ህገ መንግሥታዊ ወንጀሎች ችሎት በፃፉት ደብዳቤ ከዛሬ ጀምሮ በፍቃዳቸው ችሎት ላይ ለመቅረብ እንደማይችሉ ገለፁ።

 አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ጸረ ሽብርና ህገ መንግሥታዊ ወንጀሎች ችሎት በፃፉት ደብዳቤ ከዛሬ ጀምሮ በፍቃዳቸው ችሎት ላይ ለመቅረብ እንደማይችሉ ገለፁ።

በደብዳቤያቸው ላይ ፤ "መንግስት ከፊቱ ይጠብቀው ከነበረው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከወዲሁ ለማስወገድ አስቀድሞ ወጥኖ በነበረው ዕቅድ መሠረት የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ በማሳበብ እሥር ቤት ካጎረን እነሆ አንድ አመት ሆኖታል" ብለዋል። በዚህ ጊዜ ለሀገሪቱ የፍትህ ተቋም ክብር በመስጠት የቀረበብንን ክስ ህጋዊ በሆነ መንገድ ተከራክረን ንጽህናችንን ለማረጋገጥ በችሎት እየተገኘን በትዕግስት እና አርአያነት ባለው መልኩ ህግ አክባሪ ዜጎች መሆናችንን ለማስመስከር ሞክረናል ብለዋል። ይህንን ስናደርግ የነበረው በችሎቱ ለተሰየሙት ዳኞች ፣ ለሚያጅቡን ፖሊሶች እና ለምንገኝበት ማረሚያ ቤት ተገቢውን ክብር በመስጠት ሲሆን በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ውሳኔ አስፈጻሚው የመንግስት አካል ተግባራዊ ያደርጋል በሚል ጽኑ እምነት ነበር ሲሉ ገልፀዋል። ነገር ግንበሂደቱ እንደተረዳነው ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ውሳኔ በህገወጥ መንገድ እየተጣሰ በነፃ የተሰናበቱ ዜጎች በመንግስት ኃይሎች እየተጠለፉ ወደ ሌላ እስር ቤት ሲወሰዱ አንዳንዴም ደብዛቸው ሲጠፋ ተመልክተናል ብለዋል።


ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

 ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው። ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ...